post-thumb

"የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ቢኖር ጥሩ ነው ሳይሆን ፤ የግድ መኖር ያለበት እጅግ አስፈላጊ ነው።" ሴባስቲያን ኮ

የአለም አትሌቲክስ ፕሬዝዳንት ሴባስቲያን ኮ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የፕሬዚደንት እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የምርጫ ውዝግብ እና በአጠቃላይ ከስፖርቱ ጋር በተያያዘ ተደጋግሞ ከሚነሳው የመልካም አስተዳደር ችግር ጋር በተያየዘ የሚያውቁት ጉዳይ ካለ በልዩ ስፖርት ለቀረበላቸው ጥያቄ ተከታዩን መልስ ሰጥተዋል።

“በጉዳዩ ዙሪያ በጥልቀት አስተያየት መስጠት አልችልም። ነገርግን ሁሉንም አባል ፌዴሬሽኖች የሚከታተል፤ እኔም በቅርበት አብሬው የምሰራበት የልማት እና አለምአቀፍ የግንኙነት ክፍል  አለኝ። 

ይህ ክፍል መሬት ላይ የሚሰራውን ስራ ፣ አስተዳደር አካባቢ፣ በአጠቃላይ የUN አባል ያልሆኑ ሃገራትን ጨምሮ ከ200 በላይ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖችን የስፖርት እንቅስቃሴ የሚገመግም ነው።

የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ቢኖር ጥሩ ነው ሳይሆን ፤ የግድ መኖር ያለበት እጅግ አስፈላጊ ነው። ጉዳዩ ከስፖርቱ ባሻገርም ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። አትሌቲክሱ ውስጥ በአጋርነት መስራት ለሚፈልጉ ተቋማት፤ አብረው እንዲቀጥሉ ለማድረግ መተማመንን የሚሰጥ ጭምር ነው።

ለማንኛውም የማረጋግጥልህ ነገር ቢኖር፤ ያነሳኻቸውን ስጋቶች የማስብባቸው እና አባል ብሔራዊ ፌዴሬሽኖቻችን ውስጥ ችግሮች ሲኖሩ AIU(አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት) በጣም ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ ድርጅት ነው።" ሲሉ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

 



Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

Comments

Leave a Comment

Login or register to interact with an article.